ታዳጊዎቹ ከሰሜን አፍሪካ ሀገራትና ከኤርትራ የመጡ መሆኑ የተነገረ ሲሆን አብሯቸው አንድም አዋቂ እንደሌለ ፖሊስ ገልጿል።እነዚህ ታዳጊዎች አየርላንድ ገብተው የተገኙት በተለያዩ ጊዜያት መሆኑንም ፖሊስ ገልጿል።
ታዳጊዎቹ በምን መንገድ ወደ ሰሜን አየርላንድ እንደገቡ ግልጽ ያልሆነ ሲሆን፣ ምናልባትም በመርከቦች ወይንም በእቃ መጫኛ ኮንቴይነር ተጭነው እንደመጡ ይገመታል።
ፖሊስ ግን በኮንቴይነር ነው የገቡት የሚለውን በማስተባበል ታዳጊዎቹ በምን መንገድ እንደመጡ ለማወቅ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ገልጿል።
ታዳጊዎቹ ከተገኙበት ጊዜ ጀምሮም ቤልፋስት ውስጥ በሚገኝ የጤናና ማህበራዊ እንክብካቤ በሚያደርግ ማዕከል ውስጥ እንዲቆዩ መደረጋቸው ተጠቅሷል።
የሰሜን አየርላንድ ፖሊስ እንዳለው “ከተለያዩ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ጋር በመተባበር በእንክብካቤ ማዕከል ውስጥ ያሉት ታዳጊዎች እንዴት ያለ አዋቂ ሰው ድጋፍ እዚህ ሊደርሱ እንደቻሉ ለማወቅ እየሰራን ነው” ብሏል።”ነገር ግን ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ የታዳጊዎቹ ደህንነትን ነው” ሲል አክሏል::
ቢቢሲ
COPYRIGHT@AAMMA