ዩናይትድ ስቴትስ በቻይና ዲፕሎማቶች ላይ እገዳ መጣሏ ተገለፀ፡፡
በዚህ መሠረት የቻይና ዲፕሎማቶች ከፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ጋር ከመገናኝታቸው በፊት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ በዲፕሎማቶቹ ላይ እገዳ የጣለችው ቀደም ሲል በቻይና በኩል ለተፈፀመው ተመሳሳይ ድርጊት የአጻፋ ምላሽ መሆኑን ዘገባው አስታውቋል፡፡
አንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣን በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
በቻይና የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቶች በትምህርት ተቋማትና በምርምር ማዕከላት ተገኝተው ስራቸውን እንዳያከናውኑ እገዳ ተጥሎባቸዋል፤ በዚህም መሠረት እኛም ተመሳሳይ የሆነ ውሳኔ ወስደናል ብለዋል እኚሁ ባለስልጣን፡፡
ቀደም ሲልም እነዚህ የዓለማችን ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ሀገራት የንግድ ጦርነታቸውን አጧጡፈው መቀጠላቸው ይታወሳል፡፡
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ጉዳይ የተናጠል ስምምነት እየተዘጋጀ መሆኑን ነው ያመለከቱት፡፡
ከአሁን በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ የቻይና ዲፕሎማቶች ማንኛውንም የሀገሪቱ ባለስልጣን ከማግኘታቸውና ዩኒቨርስቲዎችን ከመጐብኝታቸው በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን እውቅና ማግኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡
አልጀዚራ
COPYRIGHT@AAMMA