አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (ኤኤምኤን) ሃምሌ 6 2011 ዓ.ም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በተገኙበት በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 9 ሺህ 637 ተማሪዎች ዛሬ አስመረቀ።
በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ባደረጉት ንግግር ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ጠ/ሚሩ በንግግራቸው ዩኒቨርስቲዎች የምርምር እና የተለያዩ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩባቸው ናቸው ብለዋል፡፡በተጨማሪም ተመራቂዎች ጠንክረው በመስራት የሃገራቸውን ብድር መክፈል ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ጠ/ሚሩ፡፡
ዩኒቨርሲቲው በ10 ኮሌጆችና 12 ትምህርት ቤቶቹ ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን ሲሆን ከእነዚህም 2 ሺህ 763 ሴቶች መሆናቸውም ታውቋል።
ዩኒቨርሲቲው 5876 ተማዎችን በመደበኛ ፕሮግራም፣ የቀሩትን 3761 ተማሪዎችን ደግሞ በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ያስመረቀ ሲሆን ከእነዚህም 230ዎቹ በሶስተኛ ድግሪ የተመረቁ ናቸው።
ከእነዚህም 2 ሺህ 85 ተማሪዎችን በማታ ፕሮግራም፣ 319 ተማሪዎችን በርቀት እንዲሁም 1 ሺህ 995 ተማሪዎችን ደግሞ በክረምት ፕሮግራም የተማሩ ናቸው፡፡
በተጨማሪም ለአገሪቷ ሰፊ ግልጋሎት በመስጠት ለሚታወቁት ለተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እንዲሪስ እና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም የክብር ዶክተሬት ማዕረግ ሰጥቷል።
COPYRIGHT@AAMMA