ቡድኑ ለምርጫው የመንግስቱን ሀብት ተጠቅሟል ሲል ገዢው ፓርቲ ፍሬሊሞን ከሷል፡፡ የምርጫው ሂደት በስፋት ሁከት የታየበት እንደነበርም ገልጿል፡፡
የእለተ ማክሰኞው ፕሬዝዳንታዊ ፓርላማዊ እና ክልላዊ ምክርቤቶች ምርጫ ውጤት እስካሁን ይፋ ባይሆንም የውጤቱ መገለጽ በገዢው ፓርቲና የቆየው ተቀናቃኙ ተቃዋሚው ሬናሞ መካከል የተፈረመውን ዋዣቂ የሰላም ስምምነት አደጋ ላይ ሊጥለው እንደሚችል ተፈርቷል፡፡
የአውሮፓ ህብረት መግለጫም የወጣው ሁለት ወር ያስቆጠረው የሰላም ስምምነት ምርጫው ችግር እንደነበረበትና መጭበርበሩን የሚገልጹ ሪፖርቶች እንዳያውኩት በተሰጋበት ወቅት ነው፡፡
ይሁን እንጂ ገዢው ፓርቲ የቀረበበትን ወቀሳ መሰረተ-ቢስ ሲል የህብረቱን መግለጫ ውድቅ አድርጓል፡፡
የአውሮፓ ህብረት ትልቅ ስህተት ፈጽሟል ያለው ፍሬሊሞ በምርጫው ሂደት ጥቅም ላይ ያዋልኩት የገዛ ሀብቴን ነው ሲል ህብረቱን መኮነኑም በአልጀዚራ ዘገባ ተጠቅሷል፡፡
COPYRIGHT@AAMMA