በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተዘጋጀው የመደመር መጽሐፍ ምረቃ ህዳር 13 ቀን 2012 ዓ.ም በኬንያ ናይሮቢ ይካሄዳል።
በኬንያ ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ከናይሮቢ የኢፌዴሪ ኤምባሲ የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሞ ዝግጅት እየተደረገ ነው።
በምረቃው ላይ ኢትዮጵያውያን የኬንያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና መቀመጫቸው ናይሮቢ ያደረጉ አምባሳደሮች የሚሳተፉ ሲሆን በመጽሐፉ ዙሪያም ገለጻ ይደረጋል።
ዶ/ር አብይ አህመድ መጽሐፍ በውጭ አገር ከሚመረቅባቸው ሁለት ሀገሮች ውስጥ ኬንያ አንደኛው ነው።
የመጽሐፍ ምረቃው እንዲሳካ ኤምባሲው እና በኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በጋራ እየሰሩ ከመሆናቸውም በላይ የተለያዩ የኬንያ ተቋማት ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን በኬንያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
COPYRIGHT@AAMMA