የአሜሪካዋ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰር ከነገ ቅዳሜ ጀምሮ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ይገባሉⵆ
ከ50 በላይ የንግድ ማህበረሰብ አባላትም ከከንቲባዋ ጋር አብረው ይመጣሉ፡፡
ከንቲባዋ በአዲስ አበባ ቆይተቸው አዲስ አበባና ዋሽንግተን ዲሲ የእትማማች ከተማነት ስምምነታቸውን በአዲስ መልክ ለማደስ የሚያስችላቸው ስምምነትም ያደርጋሉ፡፡ ከንቲባዋ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት ከዚህ ቀደም ኢ/ር ታከለ ኡማ በዋሽንግተን ዲሲ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ባቀረቡላቸው ጥሪ መሰረት ነው፡፡
ከንቲባዋ በአዲስ አበባ ቆይታቸው በተለያዩ ተቋማት ጉብኝትና ውይይት የሚኖራቸው ይሆናል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
COPYRIGHT@AAMMA