የኢሬቻ ባዛር እና ኤግዚቢሽን በይፋ ተከፈተ፡፡
አዲስ ሚድያ ኔትወርክ (ኤ ኤም ኤን) መስከረም 19፤2012የኢሬቻ ባዛር እና ኤግዚቢሽን የአሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ እና የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው በተገኙበት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በይፋ ተከፍቷል።
በዛሬው ዕለት የተከፈተው ባዛር እና ኤግዚቢሽኑ ከዛሬ ጀምሮ ለአሥር ተከታታይ ቀናት የሚቆይ መሆኑን ከኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እና በቢሾፍቱ ሆራ ሀርሰዴ የፊታችን መስከረም 24 እና 25 2012 እንደሚከበር ይታወቃል።
COPYRIGHT@AAMMA