ኢ/ር ታከለ ኡማ በአቃቂ ቃሊቲ ከ15 ዓመት በላይ ምላሽ ሳያገኙ ለቆዩ 539 ነዋሪዎች የቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ሰጥተዋል፡፡
ነዋሪዎቹ በተለያዩ አደጋዎችና በተለያዩ ምክንያቶች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተነስተው የነበሩ ነዋሪዎችናቸው፡፡
539 የሚሆኑ ነዋሪዎች ነው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተሰጣቸው፡፡
ነዋሪዎቹ ከቂርቆስና ከተለያዩ አካባቢዎች በደረሱ አደጋዎችና የተለያዩ ምክንያቶች ከመኖሪያቸው የተነሱና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ መኖር የጀመሩ ናቸው፤ሆኖም ከ15 አመታ በላይ የይዞታ ማረጋገጫ ሳይሰጣቸው በመቆየታቸው ቅሬታቸውን ለአመታት ሲያሰሙ ቆይተዋል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ በመገኘት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታውን ለነዋሪዎቹ ያስረከቡት ኢ/ር ታከለ ኡማ “የዓመታት ጥያቄያችሁን እንደ ከተማ አስተዳደር ለመመለስ ያደረግነው ጥረት በመሳካቱ እና እናንተም የቤት ባለቤት ስለሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ!” ብለዋል፡፡
COPYRIGHT@AAMMA