በፓሪስ ፈረንሳይ በመካሄድ ላይ ባለው የፊፋ የሴቶች እግር ኳስ ስብሰባ ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የሴቶች እግር ኳስ እድገት እየታየበት ቢሆንም የወንዶችን ያህል ግን መዋዕለ ንዋይ እየፈሰሰበት እንዳልሆነ ገልጸዋል።በሴቶች ስፓርት ላይ ብዙ መስራት እንደሚገባም የተናገሩት ፕሬዝዳንቷ የሴቶቸን የስፖርት ተሳትፎ ለማሰደግ የምናፈሰው መዋዕለንዋይ በአንድ መቶ እጥፍ መልሶ እንደሚከፍለን እርግጠኛ ነኝ ሲሉ ተናግረዋል።ምክንያቱም ደግሞ ሴቶች ማድረግ ይችላሉና ያሉት ፕሬዝዳንት ሳህልወርቅ ይህን ካደረግን ለውጥ ማምጣት ይቻላል ሲሉ ማስግንዘባቸውን ከፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመልክታል።
COPYRIGHT@AAMMA