አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2012 ) የአፍሪካ ሀገራት እና መንግስታት መሪዎች እንዲሁም የሌሎች ሀገራት መሪዎች ለአፍሪካ ህብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ ከትናንት ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ነው።
እስካሁንም የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ፣ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌህ እና የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ከዚህ ባለፈም የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ሙሃመዱ ቡሃሪ ምሽቱን አዲስ አበባ ደርሰዋል።
በተጨማሪም የካናዳ እና የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትሮች እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል።
መሪዎቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
33ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የፊታችን እሁድ እና ሰኞ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ከዚያ ቀደም ብሎ የህብረቱ የስራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ትናንት ተጠናቋል።
ጉባኤው “ግጭትና ጦርነትን በማስቆም ለአፍሪካ ልማት ምቹ ሁኔታን ማመቻቸት” በሚል መሪ ቃል ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው።
ለጉባኤው ከህብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች በተጨማሪ የተመድ ዋና ፀሃፊ እና የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ ድርጅቶች ሀላፊዎች ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ።
You must be logged in to post a comment.
COPYRIGHT@ADDIS MEDIA NETWORKAMN